Fana: At a Speed of Life!

የመከላከያ ሰራዊት ፋውንዴሽን ያለውን ሚና ይበልጥ ማጠናከር ይገባል – ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 1፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ የመከላከያ ሰራዊት ፋውንዴሽን ያለውን ሚና ይበልጥ ማጠናከር ይገባል አሉ።

ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ በመከላከያ ሠራዊት ፋውንዴሽን ስር እየተካሄዱ ያሉ የአዳማ ጋርመንትና ኢንዱስትሪ፣ የጋሻ የሠራዊቱ የጋራ መኖሪያ ቤቶች ፕሮጀክት እና የመከላከያ ባጅና ሜዳሊያ ማምረቻ ፋብሪካን ጎብኝተዋል።

በጉብኝቱ ወቅት የአዳማ ጋርመንት ኢንዱስትሪ ያስገነባውን አዲስ የማስፋፊያና የማሻሻያ ፕሮጀክት በይፋ መርቀው ከፍተዋል።

በጋሻ መኖሪያ ፕሮጀክት፣ በአዳማ ጋርመንት ኢንዱስትሪ እንዲሁም በመከላከያ ባጅና ሜዳሊያ ማምረቻ ፋብሪካ የተከናወኑ የልማት ስራዎችንም ተመልክተዋል።

ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ በወቅቱ ባስተላለፉት መልዕክት፤ የፋውንዴሽኑን አመራሮችና ሰራተኞች በተገኘው ለውጥ ሳይዘናጉ ለበለጠ ውጤት እንዲተጉ አሳስበዋል።

በቀጣይም የምርት ጥራትን በማሻሻል፣ የምርምርና የቴክኖሎጂ ልማትን በማስፋፋት፣ የዲጂታላይዜሽን ስራዎችን በማጠናከር፣ የግብዓት አቅርቦትን በራስ አቅም በማሳደግ በአፍሪካ ደረጃ ተወዳዳሪ ኢንዱስትሪ እንዲገነባ አቅጣጫ ሰጥተዋል ሲል የመከላከያ ኦንላይን ሚዲያ ለፋና ዲጂታል ገልጿል።

ሰራዊቱ መለኪያው ሀገሩ ነው ያሉት ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ፤ የመከላከያ ሰራዊት ፋውንዴሽን የተቋሙንና የሀገሪቱን ፍላጎት በማሳካት ያለውን ሚና ይበልጥ ማጠናከር ይገባል ብለዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.