Fana: At a Speed of Life!

በሶማሌ ክልል በ2 ቢሊየን ብር ወጪ የቱሪስት ማዕከል ሊገነባ ነው

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 23፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በሶማሌ ክልል በ2 ቢሊየን ብር ወጪ ዘመናዊ የቱሪስት ማዕከል ሊገነባ መሆኑ ተገለፀ፡፡

በሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተደድር ሙስጠፌ መሀመድና በመከላከያ ሚኒስትሩ  አብርሃም በላይ (ዶ/ር) የተመራ የፌዴራልና የክልል ልዑካን ቡድን በሶማሌ ክልል ዘመናዊ የቱሪስት ማዕከል ለመገንባት የታሰበ ምቹ ቦታን ለይቷል፡፡

የቱሪዝም ልማት ፕሮጀክቱ በክልሉ ሸበሌይ ወረዳ ዙሪያ በሚገኙት ተራሮች ሥር እንደሚገነባ የተገለፀ ሲሆን÷ ለፕሮጀክቱ እስከ 2 ቢሊየን ብር ወጪ እንደሚደረግበትም ታውቋል፡፡

የቱሪስት ማዕከሉ ዘመናዊ ሆቴሎች፣ የባህል ማዕከላልና ዘመናዊ የቱሪስት ግድቦችን ያካተተ  መሆኑን ከክልሉ መንግስት ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.