Fana: At a Speed of Life!

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አነስተኛ ገቢ ላላቸው 220 ሰዎች ማዕድ አጋሩ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 5፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የፋሲካ እና የዒድ አልፈጥር በዓላትን ምክንያት በማድረግ አነስተኛ ገቢ ላላቸው 220 ሰዎች ማዕድ አጋርተዋል፡፡

በጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት የሚያገለግሉ አነስተኛ ገቢ ያላቸውን ሰራተኞች ጨምሮ በጽህፈት ቤቱ ሰራተኞች ደመወዝ መዋጮ ለሚረዱ ሕጻናት ነው ጠቅላይ ሚኒስትሩ ማዕድ ያጋሩት፡፡

በዚህም ለ220 ሰዎች በዓላቱን ምክንያት በማድረግ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በተገኙበት የማዕድ ማጋራት መርሐ ግብር መካሄዱን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.