Fana: At a Speed of Life!

 በ2018 በጀት ዓመት የኢትዮጵያ አየር መንገድ 9 ነጥብ 1 ቢሊየን ዶላር ገቢ አገኘ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 22፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በ2018 በጀት ዓመት የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ 9 ነጥብ 1 ቢሊየን ዶላር ገቢ አገኘ፡፡

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ዋና ስራ አስፈጻሚ መስፍን ጣሰው የ2018 በጀት ዓመት አፈጻጸምን በተመለከተ መግለጫ ሰጥተዋል፡፡

አቶ መስፍን ጣሰው በዚሁ ወቅት፤ 2018 በጀት ዓመት ለአየር መንገዱ የስኬት ዓመት ነበር ብለዋል፡፡

በተለይ የመዳረሻ ቦታዎችን በማስፋት ረገድ በዓለም አቀፍ ደረጃ አራት አዳዲስ መዳረሻዎችን እንዲሁም በሀገር ውስጥ ደግሞ ሶስት አዳዲስ መዳረሻዎችን ስራ ማስጀመር መቻሉን ጠቅሰዋል፡፡

‎በመካከለኛው ምስራቅ የተካሄደው ጦርነት የአየር መንገዱን ስራ ፈታኝ አድርጎበት እንደነበር ጠቁመው፤ አየር መንገዱ በተለያዩ ጫናዎች ሳይበገር የተሳካ ዓመት አሳልፏል ነው ያሉት፡፡

በዚህም አየር መንገዱ በበጀት ዓመቱ 9 ነጥብ 1 ቢሊየን ዶላር ገቢ ማግኘቱን ገልጸው፤ ይህ አፈጻጸም ካለፈው ዓመት ጋር ሲነጻጸር የ20 በመቶ እድገት ማሳየቱን አመልክተዋል፡፡

በእመቤት ሲሳይ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.