ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ከጣሊያን ጠቅላይ ሚኒስትር እና ከሶማሊያ ፕሬዚዳንት ጋር ተወያዩ
አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 7፣ 2015(ኤፍ ቢ ሲ)ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከጣሊያን ጠቅላይ ሚኒስትር ጆርጂዮ ሜሎኒ እና ከሶማሊያ ፕሬዚዳንት ሀሰን ሼክ መሐሙድ ጋር ተወያዩ።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ከሁለቱ ሀገራት መሪዎች ጋር ያደረጉት ውይይት የሶስትዮሽ ትብብርን ለማጠናከር ያለመ መሆኑ ተገልጿል።
መሪዎቹ በመሰረተልማት እና በኢኮኖሚ ጉዳዮች ላይ በጋራ መስራታቸውን አጠናክረው መቀጠል በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይም መክረዋል።
የጣሊያን ጠቅላይ ሚኒስትር ጆርጂዮ ሜሎኒ እና የሶማሊያ ፕሬዚዳንት ሀሰን ሼክ መሐሙድ ለይፋዊ የስራ ጉብኝት ትናንት አዲስ አበባ መግባታቸው ይታወቃል።