Fana: At a Speed of Life!

በ400 ሚሊየን ዶላር ወጪ 200 የገጠር ከተሞችን የኤሌክትሪክ ተጠቃሚ ለማድረግ እየተሰራ ነው

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 10፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ከዋናው ግሪድ ርቀው የሚገኙ ከ200 በላይ የገጠር ከተሞችን የኤሌክትሪክ ተጠቃሚ ለማድረግ እየሰራ መሆኑን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት አስታውቋል፡፡

አገልግሎቱ በዘርፍ ከተሰማሩ የግል ድርጅቶችና ማህበራት ጋር በመሆን በአዴል ፕሮግራም ከዋናው ግሪድ ርቀው የሚገኙ ከ200 በላይ የገጠር ከተሞችን የኤሌክትሪክ ተጠቃሚ ለማድረግ ስራ መጀመሩን ገልጿል፡፡

በተጨማሪም በብሄራዊ ኤሌክትሪፊኬሽን ፕሮግራም ከዋናው ግሪድ 65 በመቶ እንዲሁም በአማራጭ የኃይል ምንጭ 35 በመቶ የሚሆነውን የህብረተሰብ ክፍል የኤሌክትሪክ ተጠቃሚ ለማድረግ እየተሰራ ነው ተብሏል፡፡

ለፕሮጀክቱ 400ሚሊየን የአሜሪካን ዶላር አጠቃላይ በጀት የተያዘ መሆኑን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት መረጃ ያመላክታል፡፡

ፕሮጀክቱ ከዋናው ግሪድ ርቀው በሚገኙ የሀገሪቱ አካባቢዎች የሚኖሩ የህብረተሰብ ክፍሎችን ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚ ለማድረግ እና የኑሮ ሁኔታቸውን ለማሻሻል ያለመ መሆኑ ተጠቁሟል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.