Fana: At a Speed of Life!

የሱዳን ጦር እና ፈጥኖ ደረሽ ሃይሎች የ24 ስዓት ተኩስ አቁም አወጁ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 10፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የሱዳን ጦር እና ፈጥኖ ደራሽ ሃይሎች ከዛሬ ምሽት ጀምሮ ለ24 ስዓታት የሚተገበር የተኩስ አቁም ስምምነት አውጀዋል፡፡

ሁለቱ ተፋላሚ ሃይሎች የ24 ስዓት ተኩስ አቁም ያወጁት የአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን ሁለቱ ወገኖች ተኩስ አቁም እንዲያደርጉ ጫና ማድረጋቸውን ተከትሎ መሆኑን ሮይተርስ ዘግቧል፡፡

የተቁስ አቁሙ ስምምነቱ የሰብዓዊ እርዳታ ለማድረስ እና ንፁሀን ዜጎች ከጦርነት ቀጠናው ለቀው እንዲወጡ ለማስቻል አላማ ያደረገ መሆኑ ተመላክቷል፡፡

የተቁስ አቁሙ ስምምነቱ የሰብዓዊ እርዳታ ለማድረስ እና ንፁሀን ዜጎች ከጦርነት ቀጠናው ለቀው እንዲወጡ ለማስቻል አላማ ያደረገ መሆኑ ተመላክቷል፡፡

አራተኛ ቀኑን ባስቆጠረው የሱዳን ጦር እና ፈጥኖ ደረሽ ሃይሎች ግጭት እስካሁን 200 የሚደርሱ ሰዎች ሕይወት ማለፉ ተሰምቷል፡፡

እስከ ትናንት ድረስ ባለው መረጃም ለህልፈት ከተዳረጉ ዜጎች በተጨማሪ 1 ሺህ 800 ሰዎች ጉዳት ደርሶባቸዋል ነው የተባለው፡፡

የተለያዩ ሀገራት መሪዎችም ሁለቱ ተፋላሚ ሃይሎች የጀመሩትን ግጭት በማርገብ ችግሩን በውይይት እንዲፈቱ ጥሪ እያቀረቡ እንደሚገኙ ተዘግቧል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.