49ኛው የአፍሪካ ኅብረት የሥራ አስፈጻሚ ም/ቤት መደበኛ ስብሰባ በአዲስ አበባ ተጀመረ
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 21፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) 49ኛው የአፍሪካ ኅብረት የሥራ አስፈጻሚ ምክር ቤት መደበኛ ስብሰባ ዛሬ በአዲስ አበባ ተጀምሯል።
የዘንድሮው ስብሰባ “የአጀንዳ 2063 ግቦችን ለማሳካት ዘላቂ የውሃ አቅርቦትንና ደህንነቱ የተጠበቀ የንፅህና ሥርዓትን ማረጋገጥ” በሚል መሪ ሀሳብ እየተካሄደ ይገኛል።
ለሁለት ቀናት በሚካሄደው ስብሰባ የኅብረቱ አባል ሀገራት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮችና ከፍተኛ ተወካዮች በአህጉሪቱ የልማትና የትብብር አጀንዳዎች ላይ ይመክራሉ።
በተጨማሪም የአጀንዳ 2063 አፈጻጸም፣ የ2026 የአፍሪካ ኅብረት መሪ ቃል አተገባበር እንዲሁም የኅብረቱ ስምምነቶችና ሕጋዊ ሰነዶችን የሚያጸድቁ ሲሆን፥ የአፈጻጸም ሂደትን የሚመለከቱ ሪፖርቶችን እንደሚመረምሩ ይጠበቃል።
ከዚህ ባሻገር በተለያዩ አህጉራዊ ጉዳዮች ላይ ለኅብረቱ የመሪዎች ጉባኤ የሚቀርቡ ሀሳቦችንና ረቂቅ ውሳኔዎችን ያጸድቃሉ።
በመሳፍንት ብርሌ