Fana: At a Speed of Life!

በየመን ዋና ከተማ እርዳታ ሲከፋፈል በተፈጠረ መተፋፈግ የ78 ሰዎች ሕይወት አለፈ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 12፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በየመን ዋና ከተማ ለረመዳን እርዳታ ሲከፋፈል በተፈጠረ መተፋፈግ የ78 ሰዎች ሕይወት ማለፉ ተሰምቷል፡፡

አደጋው የረመዳንን የመጨረሻ ቀናት አስመልክቶ በአንድ ትምህርት ቤት ውስጥ እርዳታ ሲታደል  በተፈጠረ መጨናነቅ የተፈጠረ መሆኑ ተመላክቷል፡፡

በቦታው ለአንድ ሰው 9 ዶላር የሚጠጋ ገንዘብ ለመቀበል በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች በተጨናነቀ ሁኔታ በትምህርት ቤት ውስጥ ተሰባስበው እንደነበር ነው የተገለጸው፡፡

በሃውቲ ቴሌቪዥን የተላለፈው ተንቀሳቃሽ ምስል እንደሚያሳየው በመቶዎች የሚቆጠሩ እና ለበጎ አድራጎት የተሰበሰቡ  የመናውያን በተፈጠረው ክስተት ሲጮሁ እና ሲተፋፈጉ ተስተውለዋል፡፡

የዓይን እማኞች ለአሶሼትድ ፕሬስ የዜና ወኪል  እንደተናገሩት ÷ የሃውቲ ታጣቂዎች ሁኔታውን ለመቆጣጠር ወደ አየር መተኮሳቸውን ተከትሎ የአሌክትሪክ ሽቦ በመፈንዳቱ መተፋፈግ እና እርስ በርስ መገፋፋት በመፈጠሩ በአካባቢው በነበሩ ሰዎች ጉዳት ደርሷል፡፡

የሃውቲ የሀገር ውስጥ ጉዳይ  ቃል አቀባይ ብሪጅ አብደል-ካሌቅ አል አግሪ  በበኩላቸው÷ የረመዳን የሰብዓዊ እርዳታ መርሐ ግብሩ ከአካባቢው ባለስልጣናት ጋር ባለመግባባት እየተከናወነ እንደነበር አንስተዋል፡፡

በተፈጠረው አለመግባባትም አሳዛኝ ክስተት መፈጠሩን ነው ያስረዱት፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.