Fana: At a Speed of Life!

በብሔራዊ ምክክር አስፈላጊነት ዙሪያ የሚመክር ጉባኤ በሐረር ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 18፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የሰላም ሚኒስቴር በብሔራዊ ምክክር እና በሰላም አስፈላጊነት ዙሪያ የሚመክር ጉባኤ በሐረር ከተማ አካሂዷል፡፡

በመድረኩ የተገኙት የሠላም ሚኒስትር ዴዔታ ታዬ ደንዳአ÷በኢትዮጵያ ሊካሄድ የታሰበውን ሀገራዊ ምክክር ለማሳካት  ከትናንት መማር እንደሚገባ ተናግረዋል፡፡

መልካም የሆኑ የሠላም እሴቶችን በማስቀጠል ሀገራዊ መግባባት ላይ መስራት እንደሚያስፈልግም አጽንኦት ሰጥተዋል፡፡

የምክክር ሒደቱን ስኬታማ ለማድረግና ዘላቂ ሰላምን ለማስፈንም ባሕላዊ የእርቅ እሴቶችን ማጎልበት እንደሚያስፈልግ ጠቁመዋል፡፡

የሐረሪ ክልል የሰላምና ፀጥታ ቢሮ ሃላፊ አቶ ጥላሁን ዋደራ በበኩላቸው÷ በኢትዮጵያ ዘላቂ ሰላምን ለማጽናት መወያየትና መመካከር እንደሚገባ አንስተዋል።

በውይይት መድረኩ ሰላምን የተመለከቱ ጥናታዊ ፅሑፎች በምሁራን ቀርበው ውይይት ተደርጎባቸዋል።

በመድረኩ በሐረሪ ክልል የሚገኙ የሃይማኖት አባቶች፣ የሀገር ሽማግሌዎችና አባገዳዎች፣ ወጣቶችና ሌሎች የህብረተሰብ ክፍሎች ተሳትፈዋል፡፡

በምንያህል መለሰ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.