Fana: At a Speed of Life!

የአዲስ አበባ መምህራንና የዘርፉ አመራሮች በመዲናዋ የተገነቡ ፕሮጀክቶችን ጎበኙ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 22፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ ከተማ በሚገኙ ትምህርት ቤቶች የሚያስተምሩ መምህራንና የትምህርት አመራሮች በመዲናዋ የተገነቡ የተለያዩ ፕሮጀክቶችን ጎብኝተዋል።

መምህራኑ በለሚ ኩራ ክ/ከተማ በመገንባት ላይ የሚገኘውን የገበያ ማዕከል፣ መገናኛ አከባቢ በመገንባት ላይ ያለውን የትራፊክ መቆጣጠሪያ ማዕከል እንዲሁም አብርሆት ቤተ መጻሕፍት እና ወዳጅነት ፓርክን ጎብኝተዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ ትምህርት ቢሮ ምክትል  ኃላፊ አሊ ከማል ÷ጉብኝቱ በዋናነት መምህራን በሀገር ግንባታ ሒደቱ የሚያበረክቱትን አስተዋጽኦ አጠናክረው እንዲቀጥሉ ለማስቻል ያለመ መሆኑን ገልፀዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ መምህራን ማህበር ፕሬዚዳንት ድንቅአለም ቶሌሳ በበኩላቸው ÷በመርሐ ግብሩ መምህራን ያፈሯቸው ባለሙያዎች ከፍተኛ ፕሮጀክቶችን ገንብተው በመመልከታቸው መደሰታቸውን ተናግረዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.