“ሰኔና ሰኞ” ድራማ ግንቦት 1 በፋና ቴሌቪዥን መታየት ይጀምራል
አዲስ አበባ ፣ ሚያዝያ 25 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) “ሰኔና ሰኞ” ድራማ ግንቦት 1 ቀን 2015ዓ.ም በፋና ቴሌቪዥን መታየት ይጀምራል፡፡
ድራማውን አስመልክቶ የፕሮዳክሽን አባላትና ተሳታፊ ተዋንያን እንዲሁም የፋና ቴሌቪዥን የማኔጅመንት አባላት በተገኙበት ዛሬ በመልካ ሆቴል መግለጫ ተሰጥቷል ።
በመግለጫው የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ አድማሱ ዳምጠዉ ÷ ፋና ቴሌቪዥን የተመልካቾቹን ፍላጎት ለማርካት ከትምህርታዊ ዝግጅቶችና ከመረጃ ባሻገር በተለያዩ የመዝናኛ አማራጮች እየሰራ ይገኛል ብለዋል ።
ለባለሙያዎች መድረክ ለመፍጠር ፣ ጥበብን ለማበረታታትና የተመልካችን ፍላጎት በይበልጥ ለማሟላት አዲስ ተከታታይ ድራማ መቅረቡንም ነው የተናገሩት።
“ሰኔና ሰኞ” የሚል መጠሪያ በተሰጠው በዚህ ተከታታይ ድራማ ላይ ከ100 በላይ ተዋንያን የተሳተፉበት ሲሆን÷ እንግዳሰዉ ሀብቴ (ቴዲ) ፣ ቃልኪዳን ታምሩ ፣ ሰለሞን ሙሄ ፣ሱራፌል ብስራት (አቡ ) እና ሌሎችም ዝነኛ ተዋንያን ይጠቀሳሉ።
ድራማው በ”ኢስተም ኢንተርቴይመንት” ተዘጋጅቶ የበረበ ሲሆን÷ በማህበረሰቡ የዕለት ተዕለት የህይወት ገጠመኞች ላይ ትኩረቱን አድርጎ በዋናነት ጭብጡን በህገወጥ የገንዘብ ዝውውር ላይ አድርጎ በአስተማሪና በአዝናኝ ትዕይንቶች ታጆቦ በ አራት ምዕራፎች እና በ60 ክፍል ለተመልካቾች የሚቀርብ ነው።
ድራማው በፋና ቴሌቪዥን ግንቦት1ቀን 2015ዓ.ም ማክሰኞ 3 ሰዓትከ10 ላይ መታየት እንደሚጀምር በመግለጫው ተመላክቷል፡፡
በቀጣይነትም ድራማው በተገለፀው ቀን እና ሰዓት ይተላለፋል።
በምንተስኖት ሙሉጌታ