Fana: At a Speed of Life!

ለጄኔራል መኮንኖች የተገነቡ የጋራ መኖሪያ ቤቶች በዕጣ ተላለፉ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 25፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የመከላከያ ሰራዊት ፋውንዴሽን ለጄኔራል መኮንኖች ያስገነባቸውን የጋራ መኖሪያ ቤቶች በዕጣ አስተላለፈ፡፡

የዕጣ አወጣጥ መርሐ ግብሩ የተከናወነው÷ የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ እና የመከላከያ ሚኒስትር ዴኤታ ማርታ ሉዊጂ፣ ጄኔራል መኮንኖች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት ነው፡፡

ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ በዚሁ ወቅት ባደረጉት ንግግር÷ ሀገሩን በቅንነትና በታማኝነት እያገለገለ ላለው ሰራዊት በየደረጃው የቤት ተጠቃሚ የማድረግ ሥራ ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል፡፡

መከላከያ በሕገ መንግስቱ መርህ መሠረት የሀገርን ሰላም እና ደኅንነት በመጠበቅ ረገድ ተልዕኮውን እየተወጣ መሆኑንም አስገንዝበዋል፡፡

ቤቶቹ የተላለፉት 20 ከመቶ ቅድመ ክፍያ ለከፈሉ፣ አሁን በሥራ ላይ ላሉና በክብር ለተሰናበቱት ጄኔራል መኮንኖች መሆኑን የመከላከያ ሠራዊት መረጃ ያመላክታል፡፡

የመከላከያ ሰራዊት ፋውንዴሽን ዋና ስራ አስፈፃሚ ብር ጋዲየር ጄኔራል ደረጀ መገርሳ በበኩላቸው በግንባታ ላይ የሚገኙ ቤቶች መኖራቸውንና የማጠናቀቅ ስራው ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ጠቁመዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.