82ኛው የዐርበኞች የድል መታሰቢያ በዓል እየተከበረ ነው
አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 27፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) 82ኛው የዐርበኞች የድል መታሰቢያ በዓል እየተከበረ ነው።
በዓሉ አራት ኪሎ በሚገኘው የዐርበኞች ሃውልት ዙሪያ ነው በተለያዩ ዝግጅቶች እየተከበረ የሚገኘው ።
በአከባበር ሥነ-ሥርዓቱ የጥንታዊት ኢትዮጵያ ጀግኖች ዐርበኞች ማህበር አባላት እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።
በዓሉን ምክንያት በማድረግም ንጋት ላይ መድፍ ተተኩሷል።
በመሳፍንት እያዩ