በኡባ ደብረ ጸሃይ ወረዳ በደረሰ የጎርፍ አደጋ የ12 ሰዎች ሕይወት አለፈ
አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 27፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በጎፋ ዞን ኡባ ደብረጸሃይ ወረዳ ዛባ ከተማ የጣለው ከባድ ዝናብ ባስከተለው ጎርፍ እስካሁን የ12 ሰዎች ሕይወት ማለፉ ተገልጿል፡፡
የዞኑ ኮሙንኬሽን ጉዳዮች መምሪያ ኃላፊ ካሳሁን አባይነህ እንደገለጹት÷ በኡባ ደብረጸሃይ ወረዳ ዛባ ከተማ ትናንት ምሽት የዘነበው ከፍተኛ ዝናብ ባስከተለው ጎርፍ እስካሁን የ12 ሰዎች ሕይወት አልፏል።
በአደጋው በርካታ መኖሪያ ቤቶች የፈራረሱ ሲሆን፥ ለጊዜው ግምቱ ያልታወቀ ንብረት እንደወደመ መናገራቸውን ደሬቴድ ዘግቧል፡፡
አሁን ላይ የአስክሬን ፍለጋው ተጠናክሮ መቀጠሉን ጠቁመው÷ የሟቾች ቁጥር ሊጨምር እንደሚችልም አመላክተዋል።