Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮጵያ የመልሶ ግንባታና ማቋቋም ዕቅድ እንዲሳካ  ድጋፍ እንደሚያደርግ የተመድ የልማት ፕሮግራም  ገለጸ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 24፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ በግጭት የተጎዱ አካባቢዎችን መልሶ ለመገንባትና ለማቋቋም የተዘጋጀው ዕቅድ እንዲሳካ ድጋፍ እንደሚያደርግ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የልማት ፕሮግራም ገለጸ።

መንግስት በቀጣዮቹ አምስት ዓመታት በ20 ቢሊየን ዶላር የሚተገበር ብሔራዊ ዘላቂ የመልሶ ግንባታና መልሶ ማቋቋም ዕቅድ ማዘጋጀቱ ይታወቃል።

በኢትዮጵያ የተባበሩት መንግስታት የልማት ፕሮግራም ዳይሬክተር ቱርሃን ሳላህ ÷የተመድ የልማት ፕሮግራም በግጭት የተጎዱ አካባቢዎችን መልሶ ለመገንባትና ለዕቅዱ ተግባራዊነት ለጋሽ ድርጅቶችን እና የልማት አጋሮችን የማስተባበር ስራን እንደሚሰራ አረጋግጠዋል።

በሚቀጥለው አንድ ዓመት በአማራ፣ በትግራይ እና በአፋር ክልሎች በግጭት የተጎዱ የማህበረሰብ ክፍሎችን በዘላቂነት በማቋቋም ሂደት የሚተገበር የድጋፍ ዕቅድ ማዘጋጀቱን መግለፃቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

ዕቅዱን ለመንግስት ማቅረቡን ጠቁመው ከለጋሽ ድርጅቶች ጋር በመተባበር በጦርነት የቆዩ ዜጎች ወደ መደበኛ ህይወታቸው እንዲመለሱ ለማድረግ በትምህርትና ግብርና ስራ ላይ በሚደረገው ጥረት ቀጣይነት ያለው እገዛ እናደርጋለን ብለዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.