በመዲናዋ የክረምት ትራፊክ በጎፍቃድ አገልግሎት የሚያስተባብሩ 5 ሺህ በጎፍቃደኞች የስራ ስምሪት ወሰዱ
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 25፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የክረምት ትራፊክ በጎፍቃድ አገልግሎት የሚያስተባብሩ 5 ሺህ በጎፍቃደኞች ዛሬ የስራ ስምሪት ወሰዱ፡፡
የከተማ አስተዳደሩ የህብረተሰብ ተሳትፎና በጎፍቃድ ማስተባበሪያ ኮሚሽን ስምሪቱን ሰጥቷል፡፡
5 ሺህ በጎፍቃደኞች በክረምት የትራፊክ በጎ ፍቃድ ተግባሩን እንደሚያስተባብሩም የከተማ አስተዳደሩ ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡
በስምሪት አሰጣጥ ሥነ-ስርዓቱ ላይ የተሳተፉ በጎፍቃደኞች የደም ልገሳ ፕሮግራም ማካሄዳቸውም ተገልጿል፡፡