በክረምቱ ወራት 108 ሺህ ዩኒት ደም ለመሰብሰብ መታቀዱ ተጠቆመ
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 25፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በክረምቱ ወቅት እንደሀገር 108 ሺህ ዩኒት ደም ለመሰብሰብ መታቀዱን የኢትዮጵያ ደምና ኅብረ ሕዋስ ባንክ አገልግሎት ምክትል ዋና ዳይሬክተር ሀብታሙ ታዬ ተናገሩ፡፡
የክረምት የበጎ ፈቃድ ደም ልገሳ መርሐ ግብር ማስጀመሪያ በአዳማ ከተማ መካሄዱን የጤና ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል፡፡
በመርሐ ግብሩ ማስጀመሪያ ላይ ንግግር ያደረጉት አቶ ሀብታሙ ታዬ÷ ሁሉም አካላት ለዕቅዱ ስኬት በትብብር እንዲሰሩ ጥሪ አቅርበዋል፡፡
የክረምት እና የጾም ወቅቶች የደም እጥረት እንደሚከሰትባቸው ጠቁመው÷ በደም እጥረት ሊከሰት የሚችለውን ሞት ለመቀነስ ሁኔታዎች የሚፈቅዱለት ሁሉ ደም እንዲለግስ ጠይቀዋል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!