በተለያዩ ክልሎች እና ከተማ አስተዳደሮች የ8ኛ ክፍል ፈተና እየተሰጠ ነው
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 26፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በተለያዩ ክልሎች እና ከተማ አስተዳደሮች የ8ኛ ክፍል ፈተና ዛሬ መሰጠት ተጀምሯል፡፡
በአዲስ አበባ ከተማ 75 ሺህ 100 የ8ኛ ክፍል ተፈታኞች÷ በ182 የመፈተኛ ጣቢያ እየተፈተኑ መሆኑ ተገልጿል፡፡
ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ቅኝት ባደረገበት በልደታ ክፍለከተማ በሚገኘው የተስፋ ኮከብ ትምህርት ቤት ፈተናው በሰላማዊ መንገድ እየተሰጠ መሆኑን አረጋግጧል።
በተመሳሳይ በአማራ፣ ደቡብ፣ ጋምቤላ፣ ቤኒሻንጉል-ጉሙዝ እና በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልሎች የ8ተኛ ክፍል ክልል አቀፍ ፈተና መሰጠት መጀመሩን የክልሎቹ ትምህርት ቢሮዎች አስታውቀዋል፡፡