Fana: At a Speed of Life!

ሴቶች፣ ወጣቶችና አካል ጉዳተኞች ለሀገራዊ ምክክር ስኬት ወሳኝ ሚና አላቸው – መስፍን አረዓያ (ፕ/ር)

አዲስ አበባ፣ መስከረም 24፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ ሀገራዊ የምክክር ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር መስፍን አረዓያ (ፕ/ር) ሴቶች፣ ወጣቶች እና አካል ጉዳተኞች ለሀገራዊ ምክክሩ ስኬት ወሳኝ ሚና አላቸው አሉ።
ኮሚሽኑ ‘የሴቶች፣ ወጣቶች እና አካል ጉዳተኞች ሚና ለሀገራዊ ምክክር ስኬታማነት’ በሚል መሪ ሀሳብ በሶማሌ፣ ቤኒሻንጉል ጉሙዝ እና ሐረሪ ክልሎች እንዲሁም በድሬዳዋ አስተዳደር የውይይት መድረኮች እያከናወነ ነው።
ውይይቱን አስመልክቶ መስፍን አረዓያ (ፕ/ር) እንዳሉት፤ በምክክር ሰላምን ለማረጋገጥ ሴቶችን፣ ወጣቶችን እና አካል ጉዳተኞችን በንቃት ማሳተፍ ይገባል።
ኮሚሽኑ አጀንዳ ባሰባሰበባቸው የምክክር ምዕራፎች ሴቶች፣ ወጣቶች እና አካል ጉዳተኞች በንቃት መሳተፋቸውን አስታውሰው፤ እነዚህ ባለድርሻዎች ሀገራዊ ሰላምን ለማረጋገጥ የማይተካ ሚና አላቸው ነው ያሉት።
ሀገራዊ የምክክር ሂደቱ የሚፈለገውን ውጤት እንዲያመጣም ባለድርሻዎቹ ትልቅ ኃላፊነት እንዳላበቸው ገልጸው፤ ኮሚሽኑ መድረኮችን በመፍጠር ከሴቶች፣ ወጣቶች እና አካል ጉዳተኞች ጋር ግንኙነቱን በማጠናከር እንደሚሰራ አረጋግጠዋል።
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.