Fana: At a Speed of Life!

አምባሳደር ተሾመ ቶጋ በኢትዮጵያ የሳዑዲ ዓረቢያ አምባሳደር ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 26፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የብሄራዊ ተሃድሶ ኮሚሽን ኮሚሽነር አምባሳደር ተሾመ ቶጋ በኢትዮጵያ የሳዑዲ ዓረቢያ አምባሳደር ፋህድ ኦባይድላህ አል-ሁመይድኒን (ዶ/ር) ጋር ተወያይተዋል፡፡

በውይይታቸው አምባሳደር ተሾመ የብሄራዊ ተሃድሶ ኮሚሽን የቀድሞ ተዋጊዎችን መልሶ ለማቋቋም እያከናወናቸው የሚገኙ ፕሮግራሞችን በተመለከተ ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡

በተጨማሪም አስካሁን የተከናወኑ የመልሶ ማቋቋም ስራዎች ላይ ለአምባሳደሩ ገለጻ ማድረጋቸውን የኤምባሲው  መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.