Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮ-ጅቡቲ የህዝብ ለህዝብ ግንኙነት የባቡር ጉዞ ልዑክ ፉሪ-ለቡ ባቡር ጣቢያ ደረሰ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 28 ቀን 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የቀጠናውን ትብብር የማጠናከር ዓላማ ይዞ ከጅቡቲ ናጋድ የባቡር ጣቢያ ተነስቶ በድሬዳዋና በአዳማ ከተሞች ጉብኝት ሲያደርግ የነበረው የኢትዮ-ጂቡቲ የህዝብ ለህዝብ ግንኙነት የባቡር ጉዞ ልዑክ ፉሪ-ለቡ ባቡር ጣቢያ ደርሷል፡፡

ልዑኩ ፉሪ ለቡ የሚገኘው የኢትዮ-ጅቡቲ ዋና መስሪያ ቤት ሲደርስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ብርቱካን አያኖ፣ በኦሮሚያ ክልል የሸገር ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ተሾመ አዱኛ (ዶ/ር) እና ሌሎች ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች አቀባበል አድርገውለታል፡፡

የባቡር ተጓዥ ልዑኩ በኢትዮጵያና በጅቡቲ መካከል ያለው ወዳጅነት ይበልጥ እንዲጠናከር፣ ኢኮኖሚያዊና የህዝብ ለህዝብ ትስስሩ እንዲጎለብት ሚናውን እንደሚወጣ ተገልጿል፡፡

የኢጋድ የባቡር ተጓዥ ልዑክ በጅቡቲ መንግስት፣ ኢጋድና በጅቡቲ የኢትዮጵያ ኤምባሲ አማካኝነት የተመሰተረ መሆኑን ከኢትዮ-ጂቡቲ ባቡር መስመር አክሲዮን ማህበር የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.