Fana: At a Speed of Life!

በአዲስ አበባ 2 ነጥብ 4 ሚሊየን ብር የሚገመቱ ህገ ወጥ የፊት ጭንብል እና የስንፈተ ወሲብ መድሃኒቶች ተያዙ

አዲስ አበባ ፣ ሚያዚያ 24 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ 2 ነጥብ 4 ሚሊየን ብር የሚገመቱ ህገ ወጥ የፊት ጭንብል እና የስንፈተ ወሲብ መድሃኒቶች ተያዙ።

ህገ ወጥ የፊት ጭምብሎቹና የስንፈተ ወሲብ መድሃኒቶቹን ሲያዘዋውሩ የነበሩ ስምንት ግለሰቦችን የኢትዮጵያ ምግብና መድኃኒት ቁጥጥር ባለስልጣን ከአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ጋር በመተባበር ሚያዚያ 23 ቀን 2012 ዓ.ም በቁጥጥር ስር ማዋሉን አስታውቋል።

በዚህም መስቀል ፍላዎር አካባቢ 15 ሺህ የፊት ጭንብል እና 5 የሙቀት መለኪያ ቴርሞ ሜትር እንዲሁም ፒያሣ አካባቢ 1 ሺህ ሰርጂካል ማስክ በህገ ወጥ መንገድ ሊሸጥ ሲል ተይዞ ጉዳዩ እየተጣራ ነው።

ከዚህ ባለፈም ግምቱ 17 ሺህ 500 ብር የሆነና (Vimax herbal supplement) የተባለ በባለሥልጣኑ ያልተመዘገበና ደህንነቱ ያልተረጋገጠ ህገ ወጥ ምርት ለስንፈተ ወሲብ መድሃኒት ነው በማለት በማህበራዊ ሚዲያ ሲያስተዋውቁ የነበረ አንድ ግለሰብ እጅ ከፈንጅ ተይዞ ምርመራ እየተካሄደበት ይገኛል።

የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.