Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ለትግራይ ክልል የ20 ሚሊየን ብር ድጋፍ አደረገች

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 3፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ለትግራይ ክልል የ20 ሚሊየን ብር ድጋፍ አደረገች፡፡

በድጋፍ ርክክብ መርሐ ግብሩ የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ርዕሰ መስተዳድር አቶ ጌታቸው ረዳ፣ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት እና ልዑካን ቡድኑ ተገኝተዋል፡፡

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የሰላም ልዑክ ትግራይ ክልል መዲና መቀሌ ገብቷል፡፡

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ፣ ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት፣ የሀገር ሽማግሌዎች መቀሌ አሉላ አባ ነጋ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ የትግራይ ክልል ጊዜያዊ ርዕሰ መስታድር አቶ ጌታቸው ረዳ እና የመስተዳድር ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አማኑኤል አሰፋ አቀባበል አድርገውላቸዋል።

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ እና የሰላም ልዑካኑ ከትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ርዕሰ መስተዳድር አቶ ጌታቸው ረዳ ጋር በመቀሌ አሉላ አባ ነጋ አውሮፕላን ማረፊያ ተገናኝተው መወያየታቸውን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን መገናኛ ብዙኀን አገልግሎት ሥርጭት ድርጅት መረጃ ያመለክታል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.