Fana: At a Speed of Life!

ጌዲዮን ጢሞቲዎስ (ዶ/ር) ከፈረንሳይ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 5፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቲዎስ (ዶ/ር) ከፈረንሳይ የአውሮፓና የውጭ ጉዳዮች ሚኒስትር ዴኤታ ኤሊዩኖር ካርዋ ጋር ተወያይተዋል፡፡

ከ48ኛው የአፍሪካ ኅብረት የሥራ አስፈጻሚዎች መደበኛ ስብሰባ ጎን ለጎን ባደረጉት ውይይት ላይ፥ ሚኒስትሩ በወቅታዊ ቀጣናዊና አካባቢያዊ ጉዳዮች ዙሪያ ገለጻ አድርገዋል፡፡

ፈረንሳይ በተለይም ኢትዮጵያ የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ ሥራዎች ስኬት ጠንካራ አጋር መሆኗንም አንስተዋል፡፡

ሚኒስትር ዴኤታ ኤሊዩኖር ካርዋ በበኩላቸው፥ ሀገራቸው ለኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ማሻሻያ ስኬታማነት እንዲሁም የፈረንሳይ ኩባንያዎች በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት የበለጠ ተሳታፊ እንዲሆኑ የምታደርገውን ድጋፍ አጠናክራ ትቀጥላለች ነው ያሉት፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.