ጠ/ሚ ዐቢይ (ዶ/ር) እና የኢጋድ ስብሰባ ተሳታፊዎች አረንጋዴ አሻራቸውን አኖሩ
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 3፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) እና የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት (ኢጋድ) ስብሰባ ተሳታፊዎች ችግኝ ተክለዋል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) በተገኙበት የሱዳንን ግጭት ለመፍታት የተቋቋመው የአራትዮሽ የመሪዎች ጉባኤ በአዲስ አበባ እየተካሄደ ነው፡፡
ከስብሰባው ጎን ለጎንም ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)እና የስብሰባው ተሳታፊዎች ችግኝ ተክለዋል፡፡