ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ የግብፅ ጉብኝታቸውን አጠናቀው ወደ ሀገራቸው ተመለሱ
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 6፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ እና ልዑካቸው የግብፅ ጉብኝታቸውን አጠናቀው ወደ ሀገራቸው ተመልሰዋል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ዛሬ ረፋድ ላይ በካይሮ በተካሄደው ‘የሱዳን ጎረቤት ሀገራት ጉባዔ’ ላይ ተሳትፈዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በንግግራቸው በግብፅ የተካሄደውን የመሪዎች ጉባኤ ጨምሮ በሱዳን ለተፈጠረው ቀውስ እፎይታ ለማምጣት የተጀመሩ የተለያዩ ጥረቶችን እውቅና ሰጥተዋል፡፡
በሱዳን ያለውን ግጭት ለመፍታት በኢጋድ መሪነት እና በአፍሪካ ህብረት ድጋፍ ሰጪነት የተጀመሩ ነባር ውይይቶች ጋር ማጣጣም እንደሚያስፈልግ ነው የገለጹት።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ እና ልዑካቸው የግብፅ ጉብኝታቸውን አጠናቀው ወደ አዲስ አበባ መመለሳቸውንም የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት መረጃ ያመለክታል።