ሐዋሳ እና የፖርቹጋሏ መቶዚኒዮስ ከተሞች የእህትማማችነት ስምምነት ተፈራረሙ
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 7፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ሐዋሳ እና የፖርቹጋሏ መቶዚኒዮስ ከተሞች በኢንዱስትሪ ዘርፍ የእህትማማች ከተማ ስምምነት ተፈራርመዋል።
ስምምነቱን የሐዋሳ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ፀጋዬ ቱኬና የመቶዚኒዮስ ከተማ ከንቲባ ከርሎስ ማውታ (ዶ/ር ) ተፈራርመዋል።
መቶዚኒዮስ በፖርቹጋል ሰሜናዊ ግዛት ውስጥ የምትገኝ በባህር ዳርቻ የተከበበች ውብ፣ ምቹ የኢንቨትመንትና የኢንዱስትሪ መዳረሻ መሆኗ ተጠቁሟል።
ስምምነቱ በሐዋሳ ከተማ ላለው ግዙፉ የሐዋሳ ኢንዱስትሪ ፓርክ የገበያ ትስስር መፍጠር የሚያስችል መሆኑ ነው የተገለጸው፡፡
ከዚህ ባለፈም ስምምነቱ በሁለቱ ከተሞች መካከል የኢንቨስትመንት ትስስር እንደሚፈጥር መጠቀሱን የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡