Fana: At a Speed of Life!

በኢትዮጵያ የኢኮኖሚ ሪፎርም የተመዘገቡ ውጤቶች የሚደነቁ ናቸው – የዓለም ባንክ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 21፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ኢትዮጵያ እየተገበረችው ባለው የኢኮኖሚ ሪፎርም የተመዘገቡ ውጤቶች የሚደነቁ ናቸው አሉ የዓለም ባንክ የምስራቅ እና ደቡብ አፍሪካ ቀጣና ምክትል ፕሬዚዳንት ንዲያሜ ዲዮፕ፡፡

የገንዘብ ሚኒስትር አሕመድ ሺዴ እና የብሔራዊ ባንክ ዋና ገዥ እዮብ ተካልኝ (ዶ/ር) ኢትዮጵያ እና የዓለም ባንክ ያላቸውን ትብብር ማጠናከር በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ ከምክትል ፕሬዚዳንቱ ጋር ተወያይተዋል፡፡

ሚኒስትሩ በዚሁ ወቅት በኢትዮጵያ የኢኮኖሚ ማሻሻያ ትግበራ የተገኙ ውጤቶችን በማብራራት ባንኩ እያደረገ ላለው ድጋፍ ምስጋና አቅርበዋል፡፡

በሪፎርሙ የተመዘገቡ ውጤቶችን በዘላቂነት ለማስቀጠል በተለይም የኃይል ዘርፉን ጨምሮ ቅድሚያ በሚሰጣቸው መስኮች የሚደረጉ ድጋፎችን እና ቀጣናዊ ትብብር ማጠናከር እንደሚገባ አጽንኦት ሰጥተዋል፡፡

የብሔራዊ ባንክ ዋና ገዥ እዮብ ተካልኝ (ዶ/ር) በበኩላቸው፥ በፋይናንስ ዘርፉ የተገኙ ስኬቶችን እንዲሁም የኢትዮጵያ የዓለም የንግድ ድርጅት አባልነት ሂደት ያለበትን ደረጃ አስረድተዋል፡፡

የባንኩ የምስራቅና ደቡብ አፍሪካ ቀጣና ምክትል ፕሬዚዳንት ንዲያሜ ዲዮፕ፥ በኢትዮጵያ የኢኮኖሚ ሪፎርም የተመዘገቡ ውጤቶችን አድንቀው፥ ባንኩ ለሪፎርሙ ውጤታማነት የሚያደርገውን ድጋፍ አጠናክሮ እንደሚቀጥል አረጋግጠዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.