Fana: At a Speed of Life!

ለባሕር በር ጥያቄ ምላሽ የሁሉም ኢትዮጵያዊ አሻራ …

አዲስ አበባ፣ መስከረም 21፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ኢትዮጵያ ያነሳችው የባሕር በር ጥያቄ ምላሽ እንዲያገኝ ሁሉም ኢትዮጵያዊ የድርሻውን ሊወጣ ይገባል አሉ ምሁራን።

ምሁራኑ እንዳሉት፤ ኢትዮጵያውያን ለጥያቄው ምላሽ ማግኘት አቅማቸው በሚፈቅደው ልክ አሻራቸውን ማኖር አለባቸው።

በውጭ ጉዳይ ኢንስቲትዩት የአሜሪካና አውሮፓ ጉዳዮች አማካሪ ሽመልስ ኃይሉ ከፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን ጋር ባደረጉት ቆይታ፤ ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ መጠናቀቅ ከፍተኛ ድል ነው ብለዋል።

የግድቡ መመረቅ ኢትዮጵያ ላይ ሲደረግ የነበረውን አሉታዊ ጫና የቀየረ የአሸናፊነት ምልክት ነው ሲሉ ገልጸዋል።

ከዚህ በኋላ በዓባይ ወንዝ ዙሪያ በሚኖረው የኢትዮጵያ እና የተፋሰሱ ሀገራት ግንኙነት ላይ ትልቅ ለውጥ የሚያመጣ ቋሚ ምሰሶ ነው ብለዋል።

ውስጣዊ አንድነትን በማጠናከር በትብብር መስራት ለውጤት እንደሚያበቃ ከግድቡ ድል መማር እንደሚቻል ገልጸዋል።

በትብብር መብቶቻችንን መጠየቅ ያስፈልጋል ያሉት አማካሪው፤ መብቱ ስላለን ብቻ ሌሎች አካላት እንደማይሰጡን ማወቅ ይኖርብናል ነው ያሉት።

በተጠና ስትራቴጂካዊ መንገድ ኢትዮጵያ ከባህር በር ተጠቃሚነት እንድትገለል መደረጉን ገልጸው፤ ይህንን ጉዳይ በተጠና መንገድ መፍታት እንደሚያስፈልግ ገልጸዋል።

ኢትዮጵያውያን የባህር በር ጥያቄን በልኩ ተረድተው ለጥያቄው ምላሽ የበኩላቸውን አስተዋጽኦ ለማበርከት መነሳት አለባቸው ብለዋል።

የሥነ-አመራር አማካሪ እና ፖለቲከኛው ጌትዬ ትርፌ (ዶ/ር) በበኩላቸው፤ የሕዳሴ ግድብ ዙሪያ ይነሱ የነበሩ አሉታዊ አመለካከቶች ወደ አዎንታዊነት መለወጣቸውን ተናግረዋል።

ግድቡ ለኢትዮጵያ ጉልበት እንዲሆን መደረጉ ትልቅ ስኬት እንደሆነ አንስተው፤ ድሉ ለባህር በር ጥያቄው ምላሽ ማግኘት መንገድ እንደሚከፍት ገልጸዋል።

የባሕር በር ጥያቄ ለማስፈጸም በዲፕሎማሲ እና በአስተሳሰብ ልዕልና ቀድመን መሄድ አለብን በማለት ጠቅሰው፤ ከፍ ያለ የዲፕሎማሲ ስራ መስራት እንደሚጠበቅ ጠቁመዋል።

በዮናስ ጌትነት

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.