Fana: At a Speed of Life!

ጅቡቲ ወደብ የደረሰውን የአፈር ማዳበሪያ ወደ ሀገር ውስጥ የማጓጓዙ ሥራ በቅንጅት እየተከናወነ ነው

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 9፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ጅቡቲ ወደብ የደረሰውን የአፈር ማዳበሪያ ወደ ሀገር ውስጥ የማጓጓዙ ሥራ በተቀላጠፈ መንገድ እየተከናወነ መሆኑን የኢትዮጵያ የባሕር ትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ አስታወቀ፡፡

እስካሁን 9 ሚሊየን 160 ሺህ 354 ኩንታል ወይም 916 ሺህ 35 ቶን በላይ የአፈር ማዳበሪያ ወደ ሀገር ወስጥ መግባቱ ተገልጿል፡፡

ጅቡቲ ወደብ ከደረሰው የአፈር ማዳበሪያ ውስጥም 89 ነጥብ 14 መቶ የሚሆነው ወደ ሀገር ውስጥ ገብቶ መሰራጨቱ ነው የተጠቆመው፡፡

አሁን ላይ 1 ሚሊየን 114 ሺህ 966 ኩንታል ወይም 111 ሺህ 496 ሜትርክ ቶን የአፈር ማዳበሪያ ጅቡቲ ደርሶ ወደ ሀገር ውስጥ እየገባ እንደሚገኝ ተጠቅሷል፡፡

የአፈር ማዳበሪያውን በአጭር ጊዜ ውስጥ ለአርሶ አደሩ ለማድረስ በቅንጅት እየተሠራ መሆኑን የኢትዮጵያ የባሕር ትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ መረጃ ያመላክታል፡፡

በቀሪዎቹ 15 ቀናት ውስጥም ሰባት የአፈር ማዳበሪያ የጫኑ መርከቦች ጅቡቲ ወደብ እንዲደርሱ በማድረግ ሀገር ውስጥ ለማስገባት አስፈላጊው ሥራ መጠናቀቁ ተገልጿል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.