Fana: At a Speed of Life!

የአረንጓዴ አሻራ መርሐ-ግብሩ ዘላቂ ልማትን እውን ለማድረግ ትልቅ አስተዋጽኦ ያደርጋል – አምባሳደር ዣኦ ዢዩዋን

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 10፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ እያከናወነች ያለው የአረንጓዴ አሻራ መርሐ-ግብር ዘላቂ ልማትን እውን ለማድረግ ትልቅ አስተዋጽኦ እንደሚያደርግ በኢትዮጵያ የቻይና አምባሳደር ዣኦ ዢዩዋን ገለጹ።

በአዲስ አበባ በሚገኘው የቻይና ኤምባሲ ቅጥር ግቢ ውስጥ በአንድ ጀንበር 500 ሚሊዮን ችግኝ የመትከል አካል የሆነ የአረንጓዴ አሻራ መርሐ-ግብር ተካሄዷል።

በመርሐ-ግብሩ ላይ አምባሳደር ዣኦ ዢዩዋን ኢትዮጵያ እያከናወነች ያለው የአረንጓዴ አሻራ መርሃ-ግብር ዘላቂ ልማትን የሚያግዝ መሆኑን አምባሳደር ዣኦ ገልጸዋል።

በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ጥሪን በመቀበል የኤምባሲው ማኅበረሰብ የአረንጓዴ አሻራ መርሃ-ግብር ሆኖ ታሪክ በመጋራቱ ኩራት እንደሚሰማው ተናግረዋል።

አረንጓዴ አሻራ ትውልድ ተሻጋሪ ዘርፈ-ብዙ ጥቅም እንዳለው ተናግረው፤ በሰውና በተፈጥሮ መካከል ያለውን ቁርኝት ማሳደግ የቻይና የልማት መንገድ አንድ አካል መሆኑን ገልጸዋል።

ኢትዮጵያ የምታከናውነው የአረንጓዴ ልማት ቻይና በአድናቆት ትመለከተዋለች ብለዋል።

ቻይና ለተፈጥሮ ሀብት እንክብካቤና አካባቢ ጥበቃ ትኩረት በመስጠት ዘላቂ ልማትን ለማረጋገጥ በሚደረገው ጥረት ተባብሮ ለመሥራት ቁርጠኛ መሆኗንም አመልክተዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.