Fana: At a Speed of Life!

በመዲናዋ የሆረ ፊንፊኔ ኢሬቻ በዓልን በድምቀት ለማክበር የተደረገው ዝግጅት…

አዲስ አበባ፣ መስከረም 21፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የሆረ ፊንፊኔ ኢሬቻ በዓልን በድምቀት ለማክበር አስፈላጊው ዝግጅት ተደርጓል አለ የአዲስ አበባ ከተማ ሥራ አስኪያጅ ጽሕፈት ቤት፡፡

የዘንድሮው የኢሬቻ በዓል የፊታችን መስከረም 24 ቀን 2018 ዓ.ም በሆረ ፊንፊኔ ‘ኢሬቻ ለሀገር ማንሠራራት’ በሚል መሪ ሃሳብ ይከበራል፡፡

በም/ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ሥራ አስኪያጅ ወንድሙ ሴታ (ኢ/ር) ለፋና ዲጂታል እንዳሉት÷ ኢሬቻ የሰላም፣ የፍቅር፣ የወንድማማችነትና የአንድነት በዓል ነው፡፡

በዓሉ የኦሮሞ ሕዝብ ክረምቱ በሰላም በመጠናቀቁ ሁሉን ነገር ለፈጠረ አምላክ ምስጋና የሚያቀርብበት እንደሆነም አውስተዋል፡፡

በአዲስ አበባ የሆረ ፊንፊኔ ኢሬቻ በዓል በድምቀት እንዲከበር ኮሚቴ ተዋቅሮ አስፈላጊው ዝግጅት መደረጉን ጠቅሰው፤ በዓሉ የሚከበርበትን ሥፍራ መሰረተ ልማት የማሟላት ሥራ መከናወኑን አስረድተዋል፡፡

በዓሉ የሚከበርበት ኢሬቻ ፓርክ ውብ፣ ጽዱ እና ለጉዳት ሊያጋልጡ ከሚችሉ ነገሮች ነጻ እንዲሆን ተደርጓል ነው ያሉት።

በተጨማሪም በማክበሪያ ሥፍራው አካባቢ የኤሌክትሪክ፣ የውሃ እና የሌሎች አገልግሎቶች መቆራረጥ እንዳይፈጠር መሰራቱን ጠቅሰዋል።

በመዲናዋ ወደ ኢሬቻ ፓርክ የሚወስዱ መንገዶች በማታ ለእንግዶች እንቅስቃሴ አመቺ እንዲሆኑ የመንገድ ዳር መብራቶች እንዲሟሉ ተደርጓል ሲሉም ገልጸዋል።

ሆቴሎችና ሌሎች አገልግሎት ሰጪ ተቋማት በቂ መስተንግዶ ለመስጠት ዝግጅት ማጠናቀቃቸውን ጠቅሰው፤ የበዓሉ ታዳሚዎች ወደ አዲስ አበባ ሲገቡ የከተማዋን እንግዳ ተቀባይነት የሚመጥን አቀባበል እንደሚደረግ ጠቁመዋል።

በመላኩ ገድፍ

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.