Fana: At a Speed of Life!

“በኢትዮጵያውያን አረንጓዴ ታሪክ ተሠርቷል” – ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 11፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) 500 ሚሊየን ዛፎችን በመትከል የራሳችንን ሪከርድ እንድንሰብር የቀረበውን ጥሪ ተቀብለው የወጡትን በሙሉ አመሠገኑ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በምስጋና መልዕክታቸው “አረንጓዴ ታሪክ ሠርታችኋል። አረንጓዴ ታሪክ ጽፋችኋል” ብለዋል።

የመልዕክታቸው ሙሉ ቃል እንደሚከለው ቀርቧል

” ታሪክ ሠርታችኋል

500 ሚሊየን ዛፎችን በመትከል የራሳችንን ሪከርድ እንድንሰብር የቀረበውን ጥሪ ተቀብላችሁ የወጣችሁ ሁሉ ምስጋና ይገባችኋል። አረንጓዴ ታሪክ ሠርታችኋል። አረንጓዴ ታሪክ ጽፋችኋል።

የተዛባ አየር፣ የተራቆተ ምድር ለትውልድ አናወርስም ብላችሁ፤ ጎሕ ሳይቀድ ወደ ተራሮችና ሸለቆዎች፣ ወደ ሜዳዎችና ሸንተረሮች ተሠማርታችሁ 566 ሚሊየን ዛፎች ተክላችኋል። ሪከርዳችሁን ሰብራችኋል።

በሁሉም ክልሎች፣ ዞኖችና ወረዳዎች ዛፎች ተተክለዋል። ከ9 ሺ በላይ የተለዩ ቦታዎች ተዘጋጅተው ነበር። ከ3 ሺህ 600 በላይ የሚዲያ ባለሞያዎች በመላ ሀገሪቱ ተሠማርተው ነበር። የቴሌና የግብርና ባለሞያዎች የመረጃ አያያዙ ዘመናዊ እንዲሆን ሠርተዋል። የአዲስ አበባ ታክሲዎች ነጻ ትራንስፖርት ለችግኝ ተካዮች ተሰጥተዋል። ሕጻናት፣ እናቶች፣ አባቶች፣ አካል ጉዳተኞች፣ የሃይማኖት አባቶች፣ በነቂስ ወጥተው ተክለዋል።

ኢትዮጵያውያን ዛሬ አረንጓዴ ታሪክ ሠርተዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.