Fana: At a Speed of Life!

ኤስካይ 2 አዲስ ቦይንግ 737-8 ማክስ አውሮፕላኖችን ተረከበ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 30፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ኤስካይ (አፍሪካን ስካይ) ሁለት አዲስ ቦይንግ 737-8 ማክስ አውሮፕላኖች መረከቡ ተገለጸ፡፡

አዲሶቹ የቦይንግ 737-8 ማክስ አውሮፕላኖች የነዳጅ ፍጆታ መቀነስ የሚያስችል ቴክኖሎጂ ያላቸው መሆናቸውንም የኤስካይ 40 በመቶ ድርሻ ያለው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ያወጣው መረጃ ያመላክታል፡፡

የኢትዮጵያ አየር መንገድ የአውሮፕላኖቹ የውስጥ ክፍል÷ ሰፊ እና ዘመናዊ ከመሆናቸው ባሻገር÷ የተሻሻሉ የመቀመጫ አማራጮች ያላቸው እንዲሁም መንገደኞች በበረራ ወቅት እየተዝናኑ እንዲጓዙ የሚያስችሉ ዘመናዊ የመዝናኛ ሥርዓቶች የተካተቱላቸው መሆናቸውን ጠቁሟል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.