Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያ የኢጋድ ስምምነት ወደ ትግበራ በመግባቱ የደስታ መግለጫ መልዕክት አስተላለፈች

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 8፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) ኢትዮጵያ በፈረንጆቹ 2023 የጸደቀው አዲሱ የኢጋድ ማቋቋሚያ ስምምነት ወደ ተግባር በመግባቱ የደስታ መግለጫ መልዕክት አስተላለፈች፡፡
የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ፤ ስምምነቱ በትናንትናው ዕለት ወደ ትግበራ መግባቱን ተከትሎ ለተቋሙና ለአባል ሀገራቱ የደስታ መልዕክት አስተላልፏል፡፡
ስምምነቱ ወደ ተግባር መግባቱ አባል ሀገራቱ በተቋሙ ቀጣይነትና በቀጣናው በሚኖረው ሚና ያላቸውን የጋራ እምነት ያረጋገጡበት ወሳኝ ምዕራፍ ነው ብሏል፡፡
በተጨማሪም ትብብርን፣ አንድነትንና አጋርነትን ለማጠናከር ያላቸውን የጋራ ቁርጠኝነት የሚያንጸባርቅ መሆኑን ገልጿል።
ተቋሙ 40ኛ ዓመቱን እያከበረ ባለበት ወቅት ወደ ተግባር የገባው ስምምነቱ፤ የቀጣናው ሀገራት ለሰላምና መረጋጋት እንዲሁም ቀጣናዊ ብልጽግናን ለማሳካት የበለጠ ጠንካራ የሕግ መሠረት እንደሚፈጥርም ሚኒስቴሩ አመልክቷል።
ኢትዮጵያ የኢጋድ ዋና ጸሃፊ ወርቅነህ ገበየሁ (ዶ/ር)ስምምነቱ ተግባራዊ እንዲሆን ያደረጉትን ጥረት በማድነቅ፤ ለትግበራው ውጤታማነት ቁርጠኛ መሆኗን አረጋግጣለች።
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.