ኢትዮ ቴሌኮም የ5 ጂ የሞባይል ኔትወርክ አገልግሎትን አስጀመረ
አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 4፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮ ቴሌኮም የአምስተኛው ትውልድ (5 ጂ) የሞባይል ኔትወርክ አገልግሎትን በዛሬው ዕለት በይፋ አስጀምሯል፡፡
የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ሥራ አስፈጻሚ ፍሬሕይወት ታምሩ በወዳጅነት አደባባይ በተካሄደው የማስጀመሪያ መርሐ ግብር ላይ እደገለጹት÷ የ5 ጂ ኔትወርኩ በዛሬው ዕለት በአዲስ አበባ ከተማ በ145 ስፍራዎች ተጀምሯል፡፡
አገልግሎቱ በሰከንድ እስከ 10 ጊጋ ባይት የሚደርስ ከፍተኛ ፍጥነት እንዳለውም ተናግረዋል፡፡
ይህ አገልግሎት በአዲሱ ዓመት ዋዜማ መጀመሩ አዲስ ተስፋን የሚሰንቅ ስለመሆኑም ነው የጠቆሙት፡፡
አምስተኛ ትውልድ (5 ጂ) የሞባይል ኔትወርክ አገልግሎት ቀደም ሲል በከተማዋ በተመረጡ ሥፍራዎችና በአዳማ ከተማ በሙከራ ደረጃ ተግባራዊ ሲደረግ መቆየቱንም አስታውሰዋል፡፡
#Ethiopia
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!