ጥንካሬዎችን በማስቀጠልና ስህተቶችን በማረም ለላቀ የሕዝብ ተጠቃሚነት እንሰራለን- አቶ እንዳሻው ጣሰው
አዲስ አበባ ፣ ጳጉሜን 5 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ጥንካሬዎችን በማስቀጠል እና ስህተቶችን በማረም ለላቀ የሕዝብ ተጠቃሚነት እንሰራለን ሲሉ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው ገለጹ፡፡
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የአስተዳደር እና የፖለቲካ ማዕከል ስራ ማስጀመሪያ መርሐ ግብር በሆሳዕና ከተማ ተካሂዷል፡፡
አቶ እንዳሻው ጣሰው በዚህ ወቅት÷ ጥንካሬዎችን በማስቀጠል እና ስህተቶችን በማረም ለላቀ የሕዝብ ተጠቃሚነት እንሰራለን ብለዋል።
ለመንግስት ምስረታው የሕግ አውጪ፣ የሕግ አስፈጻሚና የሕግ ተርጓሚ አካላት በጋራ ተቀናጅተው ሒደቱ ውጤታማ እንዲሆን ጉልህ ሚና እንደነበራቸው አብራርተዋል።
የክልል አደረጃጀት ሽግግሩን መልክ ለማስያዝ የ100 ቀናት እቅድ በማዘጋጀትተግባራዊ እንቅስቃሴ መጀመሩንም ጠቁመዋል።
በክልል ምስረታው የሕዝብ ለሕዝብ ትስስር እንዲጠናከር ድጋፍ ላደረጉ የፌዴራል እና ክልል ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች ምስጋና አቅርበዋል።
በአዳዲስ ማዕከላት የሚጀምሩ ቢሮዎችን በሰው ሃይል እና በቁሳቁስ የማሟላት ስራ እየተከናወነ መሆኑንም አስረድተዋል፡፡
በክልሉ ፈጣን እና ፍትሃዊ የመንግስት አገልግሎትን ለሕዝቡ ተደራሽ ማድረግ ላይ በትኩረት እንሰራለን ሲሉም አቶ እንዳሻው ተናግረዋል።
የመንግስት ሰራተኞች በተመደቡበት ማዕከላት ሲሰማሩም ሕብረተሰቡ ትብብር እንዲያደርግ ምክትል ርዕሰ መስተዳድሩ መጠየቃቸውን የክልሉ ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡