Fana: At a Speed of Life!

አይኤምኤፍ ለሞሮኮ የ1 ነጥብ 3 ቢሊየን ዶላር ብድር አመቻቸ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 9፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ዓለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም (አይኤምኤፍ) በከባድ መሬት መንቀጥቀጥ ለተመታችው ሞሮኮ በረጅም ጊዜ የሚከፈል የ1 ነጥብ 3 ቢሊየን ዶላር ብድር ማመቻቸቱ ተገለጸ፡፡

የአይኤምኤፍ ሥራ አስኪያጅ ክሪስታሊና ጆርጂዬቫ ÷ ተቋሙ ለሰሜን አፍሪካዊቷ ሀገር ሞሮኮ ያመቻቸው ብድር ሀገሪቷ በተፈጥሮ አደጋ ምክንያት ከገባችበት ችግር እንድትወጣ ይደግፋታል ብለዋል፡፡

ገንዘቡ እንዲለቀቅ የተቋሙ ቦርድ ተሰብስቦ መጽደቅ እንደሚቀረው መግለጻቸውን የቱርክ የዜና ምንጭ ዴይሊ ሳባህ ዘግቧል፡፡

ሞሮኮ በሬክተር እስኬል 6 ነጥብ 8 በደረሰ የመሬት መንቀጥቀጥ አደጋ ተመትታ ወደ 3 ሺህ የሚጠጉ ሰዎች ሕይወታቸውን ማጣታቸው እና በሺህዎች የሚቆጠሩ መቁሰላቸው ይታወሳል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.