የኢትዮጵያ ዓየር መንገድ የትምህርት ቁሳቁስና የገንዘብ ድጋፍ አደረገ
አዲስ አበባ፣ መስከረም 9፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ዓየር መንገድ ለምገባ ፕሮግራም የሚውል የ3 ነጥብ 2 ሚሊየን ብር ለአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የምገባ ኤጀንሲ ድጋፍ አደረገ፡፡
በተጨማሪም ዓየር መንገዱ 3 ነጥብ 2 ሚሊየን ብር ዋጋ ያለው ለ4 ሺህ ተማሪዎች ተደራሽ የሚሆን የመማሪያ ደብተር ድጋፍ ማድረጉን ኢዜአ ዘግቧል፡፡
የደብተር ድጋፉ በለሚኩራ ክፍለ ከተማ በሚገኘው ጨፌ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች የሚውል ነው ተብሏል፡፡
የኢትዮጵያ አየር መንገድ የምግብ እና የመማሪያ ቁሳቁስ ድጋፍ በማድረግ በትውልዱ ላይ ትልቅ አሻራውን ማሳረፉን ተናግረዋል።
ሌሎች ተቋማት፣ ባለሃብቶች እና የከተማዋ ነዋሪዎች ድጋፍ እንዲያደርጉ ኤጀንሲው ጥሪ አቅርቧል፡፡