Fana: At a Speed of Life!

በአማራ ክልል ሶስት ዞኖች የተከሰቱ የሰብል ተባዮችን ለመከላከል እየተሰራ ነው

አዲስ አበባ፣ መስከረም 15፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በአማራ በሰሜን ሸዋ፣ በኦሮሞ ብሔረሰብ እና በደቡብ ወሎ ዞኖች ላይ የተከሰቱ የተለያየ አይነት የሰብል ተባዮችን ለመከላከል ጥረት እየተደረገ መሆኑን የክልሉ ግብርና ቢሮ ገለፀ፡፡

በአካባቢዎቹ ቢጫ ዋግን ጨምሮ የግሪሳ ወፍ እና ጢንዚዛ መከሰቱ ነው የተገለጸው፡፡

ዞኖቹ በራሳቸው አቅም ለመከላከል ከሚያደርጉት ጥረት በተጨማሪ የክልል ግብርና ቢሮ እና የፌደራል ግብርና ሚኒስቴር የበኩላቸውን ድጋፍ እንዲያደርጉ ጥሪ ቀርቧል፡፡

የአማራ ክልል ግብርና ቢሮ ምክትል ሀላፊ ቃልኪዳን ሽፈራው ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደገለጹት÷ በሶስቱ ዞኖች ከ13 ሺህ ሄክታር በላይ ማሳ ላይ የተከሰተውን የተለያየ አይነት ፀረ ሰብል ለመከላከል ጥረት እየተደረገ ነው፡፡

የግሪሳ ወፍን ለመከላከልም ማደሪያውን የመለየት ስራ መጠናቀቁን ገልጸው፤ በቀናት ውስጥ የመድሀኒት ርጭት እንደሚደረግ አመልክተዋል፡፡

በተመሳሳይ ቢጫ ዋግን ለመከላከል በዩኒየኖች እና ማህበራት በኩል የሚቀርበውን መድሀኒት በትክክል መጠቀም አስፈላጊ እንደሆነ ተነስቷል።

በእሸቱ ወ/ሚካኤል

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.