Fana: At a Speed of Life!

በበዓላት ወቅት ተገቢ አገልግሎት ለመስጠት መዘጋጀቱን የአዲስ አበባ ቄራዎች ድርጅት አስታወቀ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 15፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በበዓላት ወቅት ተገቢ አገልግሎት ለመስጠት ዝግጅት ማጠናቀቁን የአዲስ አበባ ቄራዎች ድርጅት አስታውቋል፡፡

የድርጅቱ የህዝብ ግንኙነት ሀላፊ አቶ አታክልቲ ገብረሚካኤል እንደገለጹት÷በቀጣይ ቀናት የሚከበሩ በዓላትን አስመልክቶ የአገልግሎት አሰጣጥ መዘግየት እንዳያጋጥም ዝግጅት ተደርጓል፡፡

በዓላቱ በሚከበሩበት ጊዜ የመንገድ መጨናነቅ ሊያጋጥም እንደሚችል ከግምት ውስጥ በማስገባት ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ውይይት መካሄዱንም ጠቅሰዋል፡፡

በተለይም የስጋ ስርጭት መኪኖች ያለ ችግር እንዲሰሩ ለማድረግ እየተሰራ ነው ማለታቸውን የድርጅቱ መረጃ ያመላክታል፡፡

በተመሳሳይ የአዲስ አበበ ውሃ እና ፍሳሽ ባለስልጣን በመውሊድ እና በመስቀል በዓል ወቅት የውሃ ችግር እንዳይከሰት አስፈላጊ ዝግጅት መደረጉን አስታውቋል፡፡

በዝግጅቱም የውሃ መቅጃ ሃድራንቶችን በጋራ መለየት፣ መፈተሽ እና በመምረጥ ዝግጁ የማድረግ ስራ እንዲሁም በተጠንቀቅ የሚጠብቁ የውሃ ቦቴ ተሽከርካሪ የማዘጋጀት ስራ ተጠናቋል።

ከዚህም ባሻገር ወደ መስቀል አደባባይ በሚያስገቡ በሮች የበአሉ ታዳሚዎች ውሃ በቀላሉ እንዲያገኙ ዘጠኝ ቦታዎች ላይ በርከት ያሉ የቧንቧ ውሃ ማዘጋጀቱን ተገልጿል፡፡

የውሃና ፍሳሽ ችግሮች ካጋጠሙም በነጻ የስልክ መስመር 906 ደውለው እንዲያሳውቁ ጠይቋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.