የኢትዮጵያና ሳዑዲን ግንኙነት ማጠናከር በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ ውይይት ተካሄደ
አዲስ አበባ፣ መስከረም 23፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴዔታ ብርቱካን አያኖ በኢትዮጵያ ከሳዑዲ ዓረቢያ አምባሳደር ፋሃድ ኦባይዱላህ (ዶ/ር) ጋር ተወያይተዋል፡፡
በውይይታቸውም÷ ኢትዮጵያ እና ሳዑዲ ዓረቢያ ያላቸውን የሁለትዮሽ ግንኙነት ይበልጥ ማጠናከር በሚችሉባቸው ጉዳዮች ላይ መምከራቸውን የኤምባሲው መረጃ ያመላክታል፡፡