Fana: At a Speed of Life!

ለናኖ ቴክኖሎጂ ዕድገት አስተዋጽኦ ያበረከቱ 3 ሳይንቲስቶች በኬሚስትሪ ዘርፍ የኖቤል ሽልማት አሸነፉ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 23፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) “ናኖ ቴክኖሎጂ” አሁን ያለበት ደረጃ እንዲደርስ ትልቅ ሚና ያበረከቱ 3 ሳይንቲስቶች በኬሚስትሪ ዘርፍ የ2023ን የኖቤልን ሽልማት አሸንፈዋል፡፡

ሞንጊ ባዌንዲ፣ ሉዊስ ብሩስ እና አሌክሲ ኤኪሞቭ የተባሉት የኬሚስትሪ ተመራማሪዎች የዘንድሮውን የኖቤል ሽልማት ያሸነፉት÷ በዘመናችን የምንገለገልባቸውን የቴሌቪዥን፣ የኮምፒውተርና መሰል የ”ኤል.ኢ.ዲ” መስኮተ-ርዕይ ያላቸውን ቁሶች በርተው የምንመለከታቸውን የምስል ቀለማት እንዲከስቱ የሚያስችሉ የኳንተም ነጠብጣቦችና ውኅደታቸውን በማግኘታቸው መሆኑ ተመልክቷል፡፡

ግኝታቸው በሕክምናው ዘርፍ የጭንቅላት ካንሰር ዕጢ ለመለየት በሚያስችል ቁስ ለጥቅም መዋሉም ዘ ቴሌግራፍ አስነብቧል፡፡

ተመራማሪዎቹ ያገኟቸው የኳንተም ቅንጣቶች “ናኖ ቴክኖሎጂ” አሁን ያለበት ደረጃ እንዲደርስ ትልቅ ሚና አበርክተዋል ሲል የኬሚስትሪው ዘርፍ የኖቤል ኮሚቴ በመግለጫው ጠቁሟል።

ተመራማሪዎቹ በቀጣይ በኤሌክትሮኒክስ ዘርፍ ጥቅም ላይ የሚውሉ ቅንጣቶች፣ የታዳሽ ኃይል ቁሶች ላይ የሚገኙ የኃይል መሰብሰቢያ ቅንጣቶችና በኳንተም ደረጃ የሚከወኑ የግንኙነት ቴክኖሎጂዎችን በማሻሻልና አዲስ በመፍጠር ለዓለም የበኩላቸውን እንደሚያበረክቱ ያላቸውን ተሥፋ ገልጸዋል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.