Fana: At a Speed of Life!

ስኬቶችንና ድሎችን አጠናክሮ ለማስቀጠል ፈተናዎችን በጽናት መሻገር ይገባል- አፈ-ጉባዔ ታገሰ ጫፎ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 8፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የተገኙ ስኬቶችንና ድሎችን አጠናክሮ ለማስቀጠል ፈተናዎችን በጽናት መሻገር ይገባል ሲሉ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ-ጉባዔ ታገሰ ጫፎ ገለጹ፡፡

አፈ-ጉባዔ ታገሰ ጫፎ በባህር ዳር ከተማ እየተሰጠ የሚገኘውን የብልጽግና ፓርቲ ሁለተኛ ዙር የአመራሮች ስልጠና ሒደት ተመልክተዋል።

በዚህ ወቅትም ፥ የሚስተዋሉ ችግሮችን በድል ለማለፍ ሁሉም በትብብር እና በቅንጅት ሊሰራ እንደሚገባ አጽንኦት ሰጥተዋል፡፡

ያለብንን እዳ ወደ ምንዳ ለመቀየር በሚደረገው ትግል ፈተናም፣ ስኬትም፣ ድልም ይኖራል ያሉት አፈ ጉበዔው÷ስኬቶቻችንና ድሎቻችን አጠናክሮ ለማስቀጠል ፈተናዎችን በፅናት መሻገር ይገባል ብለዋል፡፡

ተያይዘን ከሰራን ፤ ለሀገራችን ብልጽግና ከተዋደቅን ድላችን በእኛ እጅ ነው ሲሉም የተባበረና የተዳመረ ሃይል በየትኛውም ዓለም ተዓምር እንደሚሰራ አመላክተዋል።

በአሁኑ ወቅት በተለያዩ መንገዶች የሚደረጉ እንቅስቃሴዎች መልክ መልክ እንደሚይዙም አስረድተዋል፡፡

በታሪኩ ለገሰ

#Ethiopia

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television
በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.