የወል እውነትን በመያዝ ለዘላቂ ሰላም መሥራት እንደሚገባ ተመላከተ
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 11፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የሚያስተሳስሩ የወል እውነቶችን በመያዝ ለሀገራዊ አንድነት፣ ዘላቂ ሰላምና ልማት በጋራ መሥራት እንደሚገባ የሰላም ሚኒስቴር ገለጸ፡፡
“የሰላምና የሀገር ግንባታ መሰረታውያን ሀገራዊ ጥቅሞች፣ የጋራ ማንነቶች፣ ሀገራዊ እሴቶችና ሴኩላሪዝም” በሚል መሪ ሐሳብ ከሃይማኖት አባቶች፣ የሀገር ሽማግሌዎችና ባለድርሻ አካላት ጋር በአዳማ ውይይት ተካሂዷል፡፡
የሰላም ሚኒስትር ዴኤታ ታዬ ደንደአ በመድረኩ ላይ ባደረጉት ንግግር÷ በተለያዩ አጋጣሚዎች የዜጎችን አንድነት ለማላላት የሚደረጉ ሙከራዎች መኖራቸውን አንስተዋል።
የነጠላ እና ንዑሳን አጀንዳዎችን በስፋት የሚያቀነቅኑ አካላትም የግጭትና አለመረጋጋት ምክንያት በመሆን ጉዳት እያደረሱ ነው ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡
በመሆኑም የወል ትርክቶችን በማጉላት ለሀገራዊ አንድነት፣ የጋራ መግባባትና ዘላቂ ሰላም መሥራት ይጠበቅብናል ሲሉ በአጽንኦት ገልጸዋል፡፡
አንድነትን ለማጠናከር በሚደረገው ጥረት በተለይም ምሁራን፣ ፖለቲከኞች፣ የሃይማኖት አባቶችና የሀገር ሽማግሌዎች የሚጠበቅባቸውን ሚና እንዲወጡ ጥሪ ቀርቧል፡፡
የውይይቱ ተሳታፊዎች በበኩላቸው÷ ለሀገር ሰላምና ለዜጎች ደኅንነት በትብብር መሥራት የሚጠበቅብን ጊዜ አሁን ነው ብለዋል።
#Ethiopia
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!