የሕዝብን ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ ሥራዎችን አጠናክሮ ማስቀጠል ይገባል – አቶ ኦርዲን በድሪ
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 21፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የሕዝብን ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡና ውጤትን መሰረት ያደረጉ ሥራዎችን አጠናክሮ ማስቀጠል እንደሚገባ የሐረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ኦርዲን በድሪ ገለጹ።
የሐረሪ ክልል መስተዳድር ምክር ቤት የ2016 የበጀት ዓመት የመጀመሪያ ሩብ ዓመት የስራ አፈጻጸም ግምገማ ማካሄድ ጀምሯል፡፡
በመድረኩ ርዕሰ መስተዳድር ኦርዲን በድሪ÷ግምገማው በእውነት፣ በመርሕና በእውቀት ላይ የተመሰረተ እንዲሁም የህዝብ ጥቅም ማዕከል ባደረገ መልኩ ይካሄዳል ብለዋል።
ግምገማው ጥንካሬዎችን ለማስቀጠል፣ ክፍተቶችን ለማረምና በቀጣይ ተልዕኮዎችን በጋራ ለማሳካት እንደሚያግዝም ተናግረዋል፡፡
እንዲሁም የመፍትሔ አቅጣጫዎችን ለማስቀመጥ፣ የእርምት እርምጃ ለመውሰድና የአመራር ሽግሽግና ተጠያቂነትንም ጭምር ለማስፈን ይሰራል ነው ያሉት፡፡
የክልሉ ሕዝብ ተጠቃሚነትን የሚያረጋግጡ እና ውጤታማ ሥራዎችን አጠናክሮ ለማስቀጠል ጥረት ማድረግ እንደሚገባም በመድረኩ ተገልጿል፡፡
ካቢኔው በ2016 የመጀመሪያ ሩብ ዓመት የዕቅድ አፈጻጸም ላይ ግምገማና ውይይት ካደረገ በኋላ አቅጣጫ ያስቀምጣል መባሉን የክልሉ ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡