Fana: At a Speed of Life!

የአፍሪካ ሀገራት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች አዲስ አበባ እየገቡ ነው

አዲስ አበባ፣ የካቲት 3፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የአፍሪካ ሀገራት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች በ48ኛው የአፍሪካ ኅብረት የሥራ አስፈጻሚዎች ስብሰባና በ39ኛው የመሪዎች ጉባዔ ላይ ለመሳተፍ አዲስ አበባ እየገቡ ይገኛሉ፡፡

በዛሬው ዕለት አዲስ አበባ ከገቡ ሚኒስትሮች መካከል የሶማሊያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አብዲሰላም አብዲ እና የሴራሊዮን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሙሳ ቲሞቲ ካባ ይገኙበታል፡፡

እንዲሁም የሳህራዊ ዲሞክራቲክ ዐረብ ሪፐብሊክ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር መሐመድ የስልም ቤይሳት እና የሞሪታንያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሞሀመድ ሳሌም ኦድ መርዞግ አዲስ አበባ ገብተዋል፡፡

ሚኒስትሮቹ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የሥራ ኃላፊዎች አቀባበል አድርገውላቸዋል።

በተመሳሳይ የናይጄሪያ፣ የማላዊ፣ የቡሩንዲ እና የኮንጎ ሪፐብሊክ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ትናንት አመሻሽ አዲስ አበባ መግባታቸው ይታወሳል።

የኅብረቱ የስራ አስፈጻሚ ምክር ቤቱ በመደበኛ ስብሰባው ለ39ኛው የአፍሪካ ሕብረት የመሪዎች ጉባኤ የሚቀርቡ አጀንዳዎችን እንደሚያጸድቅ ይጠበቃል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.