Fana: At a Speed of Life!

ሚኒስቴሩ በውጭ ሀገር የሠራተኛ ሥምሪት ዘርፍ የሚከናወነው ሥራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ገለጸ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 21፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በውጭ ሀገር የሠራተኛ ሥምሪት ዘርፍ ከባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት የሚከናወነው ሥራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል የሥራ እና ክኅሎት ሚኒስቴር ገለጸ፡፡

የዜጎችን መብትና ደኅንነት እንዲሁም ተጠቃሚነትን ባስጠበቀ መልኩ የሚከናወነው የውጭ ሀገር የሠራተኛ ሥምሪት እንቅስቃሴ እና የቀጣይ አቅጣጫዎች ላይ ግምገማ ተካሂዷል፡፡

የሥራና ክኀሎት ሚኒስትር ሙፈሪሃት ካሚል÷ በዘርፉ የተጀመሩት ሥራዎች በጥሩ ደረጃ ላይ እንደሚገኙ ገልጸዋል፡፡

በአስፈፃሚና ባለድርሻ አካላት መካከል ያለውን የቅንጅት ሥራ በማሣደግ የተጀመሩ ሥራዎችን ማስፋት እንደሚገባ ተመልክተናል ብለዋል፡፡

ለውጭ ሀገር የሠራተኛ ሥምሪት የሚደረገው ዝግጅት የመዳረሻ ሀገራትን የገበያ ፍላጎት መሰረት ያደረገ መሆኑንም ነው በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት የገለጹት፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.