Fana: At a Speed of Life!

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 3ኛ ዓመት የስራ ዘመን 4ኛ መደበኛ ስብሰባ ላይ ከምክር ቤት አባላት ለተነሱ ጥያቄዎች በሰጡት ማብራሪያ ላይ ትምህርትና ጤናን በሚመለከት ካነሷቸው ዋና ዋና ነጥቦች መካከል፡-

👉የትምህርት ስርዓቱ ዘርፈ ብዙ ስብራት አለበት፤ ባለፉት አመታት የትምህርት ስርዓት መውደቅ ኢትዮጵያን እየጎዳ ነው ብለን ከለውጡ በፊትም ለውጥ ከጀመርንበት ጊዜም ጀምሮ ዋነኛ አጀንዳችን ይሄ ጉዳይ ነው፤

👉የትምርት ስርዓቱን ለማዳከም በጣም ጥቂት ጊዜና ስንፍና በቂ ናቸው፤ ብዙ ድካምና ብዙ ለውጥ ይፈልጋል፤ ለዚህም የመምህራንን አቅም መገንባትና የትምህርት አስተዳደር ስርዓትን ማሻሻል፤

👉የተማሪዎች ምገባ መጀመር እንዲሁም መሰረተ ልማት ማስፋፋትና የፈተና ስርዓቱን ማሻሻል ያስፈልጋል፤

👉ከፍተኛ የትምርት ተቋማት ላይ ጥራት ላይ እንስራ፣ መዋዕለ ህጻናት ላይ ቢያንስ በህዝብ ተሳትፎ ከ18 ሺህ በላይ ትምህርት ቤቶች ተገንብተዋል፤

👉መሰረቱን ካልሰራን ወደ ላይ የምናደርገው ኢንቨስትመንት ውጤታማ አያደርገንም የሚል እምነት ነበረን፤

👉ከ50 በላይ ያመጡ የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች ወደ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ይግቡ ብንልም፤ ከተቀመጠው ነጥብ ወረድ ብለን ድጋሚ የማካካሻ ፈተና ወስደው የሚያልፉት ወደ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የሚቀላቀሉበትን አሰራር እየተከተልን ነው፣

👉በትምህርት ስርዓቱ ውስጥ ያለውን ስብራት ማስተካከል ካልቻልን ልጆቻችን በህይወት ፈተና እንዲወድቁ እናደርጋቸዋለን፣ በመሆኑም በትብብር የተሻለ የትምህርት ስርዓት እንዲኖር መስራት አለብን፣

👉የ12 ክፍልን የመልቀቂያ ፈተና የወደቁ ልጆች ወድቀው ቀሩ ማለት አይደለም፤ ሀገር ቀያሪ ሐሳብ ያላቸው በርካታ ልጆች ከወደቁት መካከል አሉ፤ የተለያየ ክኅሎት ያላቸው በርካቶች አሉ፤ በቴክኒክና ሙያ ትምህርት ቤቶች የመማር አማራጭ አላቸው፡፡

👉ዛሬ የተሰሩትን የተለያዩ ዓለማችን የሚጠቀምባቸው መሣሪያዎች የፈጠሩት ብዙዎቹ ዩኒቨርሲቲ የገቡ አይደሉም፤ የእጅ ሙያ ያላቸው እና የቴክኒክና ሙያ ውጤቶች ናቸው፡፡

👉በጤናው ዘርፍ በጣም በርካታ በጅምር ያሉ ሥራዎች አሉ፤ በርካታ የሆስፒታል ግንባታዎች፣ ያሉትን የማደስ ስራዎች እየተከናወኑ ነው፡፡

👉ጤናን በሚመለከት በጥቂት ወራት ኮሌራ በኢትጵያ ውስጥ ብቻ ሳይሆን በሌሎችም ጥቂት ሀገራት ተከስቷል የወባ ወረርሽኝም እንዲሁ፤ ዋነኛ ምክንያቱም በአየር ንብረት ችግርና በመመርመሪያ ኪቶች ችግር ነበር ይህንን ለመቅረፍም ከፍተኛ ጥረት ተደርጓል፤

👉እነዚህ አይነት ወረረሽኞች ታቅዶባቸው የሚመጡ ስላልሆኑ ጉዳት ማስከተላቸው አይቀርም፤ ነገር ግን ችግሩን ለመቅረፍ ብዙ ርቀት ተኪዷል፡፡

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.